አይ.ሲስ በሊቢያ በወገኖቻቸው ላይ የፈጸመውን ግፍ ለመቃወም ሰልፍ በወጡት ላይ እስራት ተፈረደባቸው

Tewoderos_alemu_semayawi_02

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሀምሌ 7/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የ3 ወር እስራት እንደተፈረደባቸው ነገረ ኢትዮጵአ ዘገበ።

እነ ቴዎድሮስ የተፈረደባቸው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 486/ለ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ እንደሆነ የገለፀው ፍርድ ቤቱ ሆኖም ‹‹ሰሩት በተባለው ወንጀል ሰውም ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ባለመኖሩ በዝቅተኛ ወንጀል ይዘነዋል›› ብሏል፡፡ የ3 ወር እስራት ከተፈረደባቸው መካከል አንደኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ አስፋው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሆን ያሬድ ደመቀ እና አንዋር ከድር የፓርቲው አባል አለመሆናቸውን ዘገባው ይጠቅሳል፡፡ እነ ቴዎድሮስ በፖሊስ ከተያዙበት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት ወር ከሶስት ሳምንት በመታሰራቸው ከአንድ ሳምንት በኋላ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሌሎች መዝገቦችም የተለያዩ የፓርቲ አባላትና የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ጭምር ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ኤኢ.ሲስን ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላኢ አመጽ አስነስታችሁዋል በሚል በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀተሮ በተሌኤዩ ችሎቶች በመመላለስ ላኢ ናቸው።

አቶ ማሙሸት አማረ በሰልፉ ላኢ አሉ ተብለው ከመከሰስ አልፎ ዐቃቤ ሕግ የሀሰት ምስክሮች አቅርቦ ያስመሰከረ ቢሆንም በዕለቱ የምርቻ ቦርድን ከሰው ልደታ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ስለነበሩ ለፍርድ ቤቱ መከላከያ አቅርበው ፍርድ ቤቱ በአምስት ሺህ ብር ዋስትና ቢፈታቸውም ፖሊስ ውሳኔውን ሳያከብር ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውረዋል።

አቶ ማሙሸት ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም ዛሬም ድረስ ሳይፈቱ ክሱም በአይ.ሲስ ወገኖቻቸውን ወዳጡት በተለምዶ ጨርቆስ አካባቢ ለቅሶ ደርሰው ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል የፈጠራ ወንጀል መለወጡ አይዘነጋም።

ህብር ሬዲዮን ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ አድማጮች 01405770140 ደውላችሁ በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ለአስተያየቶቻችሁ 7025896347 ወይም በኢሜይል hiberradio@gmail.com ጻፉልን

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *