አርበኞች ግንቦት 7 እንደገለጸው በህወሓት አገዛዝ ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህቀደም የተንሰራፋው ዘረኝነት፣ ገደብ የሌለው ዘረፋ እና አስተዳደራዊ ግፍና በደል ያንገሸገሻቸው በርካታ አባላቱ ተዋጊ ጀቶችን እና ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን እየያዙ በተደጋጋሚ መክዳታቸው ይታወቃል፡፡ በአየር ኃይሉ ውስጥ የአባላት ኩብለላ ከምድር ኃይሉ በከፋ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ ከ40 በላይ የሚሆኑ ሞያተኛ አባላቱ ባንድ ጊዜ ከየምድቦቻቸው ተሰውረዋል፡፡ ስርዓቱን ከከዱት 40 ሞያተኛ የሆኑ የአየር ኃይሉ አባላት ውስጥ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች፣ የኮማንድ ፖስት እና የጠቅላይ መምሪያው ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡ ቴክኒሻኖች ቁጥራቸው 15 ሲሆን ምድቦቻቸው ትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ስኳድሮን፣ ሱ 27 ስኳድሮን እና አንቶኖቭ 12 ነበሩ፡፡ ከአየር ኃይል በየጊዜው ከሚከዱት ሞያተኞች ውስጥ የኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥ ሻለቃ አክሊሉ መዘነን ጨምሮ አብዛኞቹ ወደ በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ነአምን ዘለቀን ጨምሮ ከፍተኛ የግንባሩ የፖለቲካ አመራሮች ትግሉን በቅርብ በአካል በመገኘት ለመምራት ወደ ኤርትራ በረሃ መግባታቸውን ተከትሎ እርምጃው በሕዝቡ፣በሰራዊቱና ስርኣቱ በሚተማመንበት አባላት ችምር መነቃቃት መፈጠሩንና በአንጻሩ ስርዓቱ ቀንደኛ መሪዎችና ደጋፊዎች ድንጋጤ ውስጥ በመግባት ራሳቸውን ጭምር የሚያስገምት ተራ ፕሮፖጋንዳ እስከመስራት ሄደዋል።
የአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአሜሪካ ድምጽ አቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ <<ልማቱን ተዘዋውሮ ያያል ላፕቶፕ ተሰጥቶት ይጽፋል>> ማለታቸው በራሳቸው ደጋፊዎች ጭምር እአስተቻቸው እንደመጣ መረጃዎች ያሳያሉ።
ህብር ሬዲዮን በየቀኑ በድህረ ገጻችን ወይም በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።