ሰበር ዜና ፡ የአገዛዙ ፍርድ ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ከሰባት እስከ 22 ኣመት እስራት ፈረደ ፣<<.. ውሳኔው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተቀባይነት የሌለውና አለመረጋጋትን የሚጋብዝ ነው.. >> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድ

Ethiopian-Muslim-committee1

የአገዛዙ ፍርድ ቤት ላለፉት ሶስት ኣመታት በላይ ሲጓተት ለቆየው የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ዛሬ ሐምሌ27 ቀን 2007 በከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ሰሚት ምድብ በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ 18 ተከሳሾችን ዛሬ ከ7 አመት እስከ 22 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ፈረደባቸው::

በዛሬው ዕለት በካንጋሮው ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት 1.አቡበከር አህመድ 2.አህመዲን ጀበል 3.ያሲን ኑሩ 4.ካሚል ሸምሱ 5.በድሩ ሁሴን 6.ሼህ መከተ ሙሄ 7.ሳቢር ይርጉ 8.መሃመድ አባተ 9.አህመድ ሙስጠፋ 10.አቡበከር አለሙ 11.ሙኒር ሁሴን 12.ሼህ ሰኢድ አሊ ጁሃር 13.ሙባረክ አደም 14.ካሊድ ኢብራሂም 15.ሙራድ ሽኩር 16.ኑሩ ቱርኪ 17.ሼህ ባህሩ ኡመር 18.የሱፍ ጌታቸው የነበሩ ሲሆን ፍርድ በሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ብሏቸዋል:: 22 ዓመት የተፈረደባቸው 1ኛ. አቡበክር አህመድ 2ኛ.አህመዲን ጀበል 3ኛ. ያሲን ኑሩ 4ኛ. ከሚል ሸምሱ ሲሆኑ በሽብር ወንጀሉ ከፍተኛ ተሳታፊ ነበሩ ሲል ፈርዶባቸዋል:: በሌላ በኩል 18 ዓመት የተፈረደባቸው 1ኛ. ድሩ ሁሴን 2ኛ. ሳቢር ይርጉ 3ኛ. መሃመድ አባተ 4ኛ. አቡበክር አለሙ 5ኛ ሙኒር ሁሴን ናቸው:: 15 ዓመት የተፈረደባቸው 1ኛ. ሼህ መከተ ሙሄ 2ኛ. አህመድ ሙስጠፋ 3ኛ. ሼህ ሰኢድ አሊ 4ኛ. ሙባረክ አደም 5ኛ. ካሊድ ኢብራሂም ናቸው:: 7 ዓመት የተፈረደባቸው 1ኛ. ሙራድ ሽኩር 2ኛ. ኑሩ ቱርኪ 3ኛ. ሼህ ባህሩ ዑመር 4ኛ የሱፍ ጌታቸውን ናቸው:: በዛሬው ችሎት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ወደ ሲኤም ሲ ወደሚገኘው የቦሌ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎቱ ለመታደም የተጓዘ ቢሆንም ፌደራል ፖሊሶች ማባረራቸው ተዘግቧል፡፡ ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ ፍርድ ቤቱ በከፍተኛ ፖሊስ ጥበቃ ስር የነበረ ሲሆን ከቤተሰብ በስተቀር ማንኛውም ሰው ችሎቱ ውስጥ እንዳይገባ በኃይል ሰዎች ሲባረሩ እንደነበር ተጠቅሷል:: በነዚሁ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የካንጋሮው ፍርድ ቤት ከእስራት ቅጣት በተጨማሪ ተከሳሾች ይህ ውሳኔ ከፀናበት እለት ጀምሮ ለአምስት አመታት እንዳይመርጡ ፣ እናዳይመረጡ ፣ በየትኛውም ቦታ ዋስም ምስክርም እንዳይሆኑ በአጠቃላይ ከማህበራዊ መብታቸው መታገዳቸው ተዘግቧል:: ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ አለማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ተገልጿል:: የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱላቸው በሰላማዊ መንገድ ላለፉት ዓመታት ሲጠይቁ ቆይተዋል:: ፍርዱን ተከትሎ ሕዝበ ሙስሊሙ በተለያዩ ቦታዎች ሆኖ ቁጣውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::

አገዝዙ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለኮሚቴ አባላቱና ለበርካታ የህሊና እስረኞች ጥብቅና የሚቆሙትን ጠበቃ ተማም አባቡልጉን ያገደ ሲሆን ተከሳሾች ያለ ጠበቃ እንዲቀርቡ ውሳውን ባአስለውጡም ለታሪክ በችሎቱ ላይ የሚአቀርቡትን ክርክር በመፍራት የተወሰደ የበቀል እርምጃ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ የዛሬው የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ምን ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል በሚል ትላንት ከሕብር ሬዲዮ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ በንጹሃን የኮሚቴ አባላቱ ላይ ሕወሃት የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ የሚወስነው ስርኣቱ ያለበትን ጫና መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጿል። <፣…ምን አልባት ከሶስት እስከ አምስት ኣመት ሊፈረድ ሆን ተብሎ ሊፈረድ ወይም የተለመደው አይነት የጭካኔ ፍርድ ለመፍረድ መሞከር ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ተነጣጥሎ በማይኖርባት አገር በመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ላይ መፍረድ ነው ይህም ውሳኔ አለመረጋጋት ሊያመጣ ይችላል..>> ሲል ገልጻል።

ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ጨምሮ ወቅታዊ ልዩ ልዩ ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *