(ህብርሬዲዮ_ ላስ ቬጋስ) በአርባ ምንጭ ከተማ አገዛዙ የጋሞ ብሔርን ለማጥላላት በጀት መድቦ ያሳተመው መጽሐፍ ተቃውሞ መስነሳቱን ተከትሎ የቀረበበትን ተቃውሞ ለማስተንፈስ ችግሩን በሌሎች ለማሳበብ ትላንት ረቡዕ በከተማው የጠራው ሰልፍ ትላንት ሰፊ ተቃውሞ የተስተዋለበት ሲሆን ሕዝቡ ባለስልታናትን ሌባ ሌባ በማለት ንግግራቸውን በተደጋጋሚ ሲያቋርጥ ነበር። በብሄር አትክፈሉን እርስ በእርስ ለማፋጀት የምታደርጉትን ጥረት አቁሙ የሚል ግልጽ ማስጠንቀቂያ በተቃውሞው ወቅት አቅርባል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎችና ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ ሰልፈኞች በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ ሰሞኑን በተደጋጋሚ በመጽሐፉ ሳቢአ ማንነታቸው የተንቋሸሸው የጋሞ ብሄር አባላትን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በመሳተፍ በዞኑ በጀት የታተመውን የጋሞ ርዕስ የተሰጠው በአማርና ቋንቋ የተጻፈውን መጽሐፍ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ.ሕዝቡ በሰላም አብሮ መኖር የሚፈልግ መሆኑን ገልጸው ባለስልታናቱ ከከፋፋይነት ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰልፈኞቹ ማስጠንቀቃቸውን ከአርባ ምንጭ ያነጋገርናቸው የህብር ሬዲዮ ምንጮች ገልጸዋል።የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ሉሉ መሰለ በበኩላቸው ሰልፉን አስመልቶ ከስፍራው ባደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ በከተማው አስተዳደር በኩል የተጠራው ሰልፍ የተቃውሞ ድምጽ የተሰማበት እንደነበር ገልጸዋል።
በሰልፉ ላይ ተደጋግመው ከሚሰሙ መፈክሮች መካከል <<ሕግ ይከበር! ተከባብሮ ኖረውን የጋሞ ብሄር አትከፋፍሉ አታጋጩ፣ ቁጫ፣ዶርዜ እያላችሁ አትክፈሉን፣ አታጋጩን ሕዝቡ አንድ ነው፣ ጋሞን የሚያንቋሽሸውን መጽሐፍ እንዲታተም የፈቀዱ ባለስልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ የሚሉ ከተሰሙት የተቃውሞ መፈክሮች መካከል ይጠቀሳሉ።
የከተማው ከንቲባ በሰልፉ ላይ ንግግር ለማድረግ ሲወጡ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ንግግራቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ሲሆን በሁዋላ በማግባባት ሕዝቡ ተቃውሞውን ለአፍታ ገቶ ተናግረው መጨረሳቸውን እበዚሁ የህብር ምንጮች ገልጸዋል።
ህብር ሬዲዮ ጋሞ ብሄር ተወላጆች መካከል ቁጥራቸው በሺህ የሚቆጠሩ ባለፈው ቅዳሜ በዲታ ከተማ ባደረጉት ተቃውሞ ላይ በተመሳሳይ የተጻፈውን መጽሐፍ ያወገዙ ሲሆን በቃን የተጭበረበረውበን የ2007 ምርጫ አንቀበልም በራሳችን ወኪሎች እንመራለን ማለታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
ህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።