የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 10 ቀን 2007 ፕሮግራም
<…የዋሽንግተን ዲሲው ስብሰባ ሕዝቡ በቅርብ ዓመታት ከታየው የተለየ አንዳንዶች እንደሚሉት የቅንጅት ዘመንን የሚያስታውስ ነበር። የአቶ አንዳርጋቸው ፎቶ በጨረታ ከ70 ሺህ ዶላር በላይ የተሸጠበት ነው…ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በግንባር ከሰራዊቱ ጋር ሲያደርጉት የነበረው ውይይትና የሰጡት ምላሽ የሚያሳይ ፊልም ቀርቧል። ሕዝቡ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ትልቅ ድጋፉን አሳይቷል…> ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደውን ደማቅ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ስብሰባ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…እዚህ አገር ቤት ሕዝቡ መንግስት የነጻነት ታጋዮችን እውቅና ላለመስጠት የኤርትራ መንግስት ትንኮሳ ፣የሻዕቢአ ተላላኪዎች የሚለውን ፕረፖጋንዳ አልተቀበለውም። ለነጻነት ትግሉ ድጋፍ ዓለው ወታቱ መቼ ነው የምንቀላቀለው ይላል ተማሯል …ያለንበት ሁኔታ ያው ድርቅ ቢባል ይሻላል ውሃ የለም፣መብራት የለም …> አንድ የደሴ ከተማ ነዋሪ በወቅታዊ ጉዳይ አነጋግረናቸው ከሰጡን ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመደለል ይሄ ስርዓት ሲሞክር ይሄ የመጀመሪያው አይደለም። ዓላማቸው ለመከፋፈልና ለማዳከም በአገር ቤት በወገኑ ላይ የሚደረገውን ግፍ እንዳይቃወም ይህንን ለሚታገሉ እንዳይደግፍ ነበር ግን አይሳካም…ዲያስፖራ ያልማ የሚሉት ከዚህ የሚላከውን፣ከዕርዳታና ከብድር የሚወስዱትን እየዘረፉ መልሰው እያወጡ በምዕራቡ ዓለም የሚያከማቹትን ገንዘብ መጀመሪያ እነሱ ለምን አገር ቤት አያለሙበትም? ሰብኣዊ መብት የማይከበርበት፣የሕይወትና የንብረት ዋስትና በሌለበት አገር መቅደም ያለበት ነጻነት ማግኘቱ ነው…> ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የቀድሞ የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር ስርዓቱን ዲያስፖራን ለመከፋፈል ስለያዘው ያልተሳካ እቅድ ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ሁበር ማለት የሰዎችን ሕይወት ለማናጋት የመጣ በአገር ቤት በአንድ ወቅት እንደሚባለው የአየር ባየር ንግድ አይነት ዩፎዎች ናቸው የማይጨበጡ…ሁበርና ሊፍት የአንድ ሳንቲም መንታ ገጽታ ናቸው። እዚህ እኛ ሁላችንም ተባብረን በጋራ ድምጻችንን አሰምተን ባለስልጣናቱ ሰምተውናል። ከኤርፖርት እንዳይጭኑ ተከልክለው እኛም በሁለት ሳንባችን መተንፈስ ጀምረናል…> አቶ ቁምላቸው መኩሪያ ሁበርን የሚቃወሙ ኢትዮጵያን አሽከርካሪዎች በሳን ሆሴ ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለህብር ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
በኢትዮጵያ ላይ ተጋረጠው የረሀብ እና ድርቅ አደጋ አስከፊነት በዓለም አቀፍ እና ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እይታ (ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
በአገር ቤት ሕዝቡ ከኤርትራ ለሚንቀሳቀሱ የነጻነት ታጋዮች ድጋፍ እንዳለውና የአገዛዙን ፕሮፖጋንዳ አለመቀበሉ ተገለጸ
የመኢአድ የውጭ ግንኙነት በማዕከላዊ በደረሰባቸው ድብደባ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው
ከኢትዮጵያ ወደ ስዊድን የሚሰደዱት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በዕቃ መጫኛ አውሮፕላን ተሸሽጌ የገባው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀ
አዲስ አበባ ለድርድር የተቀመጡት የደቡብ ሱዳን ልዑካኖች የሕወሃት-ኢሕአዴግ አገዛዝን ዘለፉ
ከራሱ ተቃዋሚዎች ጋር ሳይደራደር ልሸምግል ማለቱን አጣጣሉት
ሶማሌዎች ሰሞኑን በኢህአዴግ ጦር ለተገደሉ ወገኖቻቸው የደም ካሳ ይከፈለን ሲሉ መንግስታቸውን ጠየቁ
ሁበርና ሊፍት በቬጋስ ስራ ለመጀመር በይፋ ማመልከቻቸውን አስገቡ
ሁበር ሰባት ሺህ ተሽከርካሪዎች ስራ ለማስጀመር እቅድ አለው
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-081615-082315