እነ አብርሃ ደስታ ከእስር በነፃ እንዲለቀቁ ተወሰነ

Yeshewas_habtamu_daniel_abreha_007

ዛሬ ሐሙስ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ መወሰኑን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ።

በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡

እነ አብርሃ ደስታ በፈጠራ የሽብር ክስ ታስረው ከፍተና መጉላላት ሲደርስባቸው መቆቱ ተደጋግሞ ተዘግቧል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *