የአረናው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ የህወሃት ባለስልታናት የስልጣን ሽኩቻ ድርጅቱን ባቻ ሳይሆን በበላይነት የሚቆጣጠረውን ኢህአዴግንም ማዳከሙ አይቀርም ሲል አስቀድሞ ለህብር ሬዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ አቅርበነዋል። በጉባኤው የተነሱ አንዳንድ ጉዳዮችን <<በህወሓት ጉባኤ እንዲህ ሆነ>> ሲል አስፍሯል።
የህወሓት ጉባኤ በሁለት ኣንጃዎች የስልጣን ሽኩቻ የጦዘ የጥሎ ማለፍ ፉክክር ተደሮጎበታል። የፖሊት ቢሮ ምርጫ ሲካሄድ የነደብረፅዮን ደጋፊ “ኣባይ ወልዱ ከሙስና የፀዳ ኣይደለም” የሚል ኣስተያየት ይሰጣል። ኣባይም “እኔ በሙስና የምጠረጠር ኣይደለሁም። እርግጥ ነው ከገቢዬ የሰራሁት ሶስት ቤቶች ኣሉኝ። ልጆቼም ጥሩ በሚባል የግል ትምህርት ቤት ኣስተምራለው። የሌሎቻቹ ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ግን ልጆቻቹ ውጭ ኣገር በከፍተኛ ክፍያ እየከፈላቹ እያስተማራቹ ነው። በሙስና ጉዳይ የያንዳንዱ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል ሰነድ በእጄ ይገኛል። ኣጣርተን ወደ ህግ እንቅረብ ካላቹ ዝግጁ ነኝ” በማለት እያንዳንዷ ባለ ስልጣን ክው ብላ ደርቃ እንድትቀር ኣድርጓል። በጣም የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ኣባይ ወልዱ በሙስና የማይመረረው እንደ ኣመራር በሶስት ቦታዎች ብቻ ፎቆች ሲሰራ የተቀረው በኣባይ ማስጠንቀቅያ ድምፁን ያጠፋው የማእከላይ ኮሚቴ ኣመራር ሁላ ምን ያህል ዘራፊ ቢሆን ነው?
የኢህኣዴግ ጉባኤው ካጠናቀቀ በሗላ በሰጠው መግለጫ ሙሰኞችና ክራይ ሰብሳቢዎች የመመንጠር ዘመቻ እንደሚያካሂድና በኣዲስ ኣበባ ዘመቻው እንደጀመረ እየገለፀ ነው።
ታድያ ኢህኣዴጎች ብቸኛው የኣብሮነታቸው መገለጫ የሆነው ሙስና ይታገላሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ኣይደለምን? በትግራይ ያለሺው የኣዲስ ኣበባ ኣንጃ ደጋፊ፣ ቀስቃሽና ኣጨብጫቢ የነበርሺው ኣመራርም ኣባልም መንገድሺን ጥረጊ። በህወሓት ቤት ሁሌ የሚታሰረው፣ የሚንገላታው ሙሰኛ ሳይሆን የተቃውሞ ድምፅ የሚያሰማ ሰው ነው። ሙስናና ህወሓት የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች ናቸው። ነፃነታችን በእጃችን ነው።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።